Your cart is currently empty!
የዋናው ቤት ስፋቱ 199.74 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ሰይፈ ገ/ፃዲቅ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ገ/ፃዲቀ ጨርቆስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/289626 በ21/3/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤ/ቁጥር አዲስ የሆነው የዋናው ቤት ስፋት 199.74 ካ/ሜ የሰርቪስ ቤቱ ስፋት 33.44 ካ/ሜ የቦታ ስፋት 233.18 ካ/ሜ መሆኑን በካርታ በውል የተፈቀደው ይዞታው ስፋት 175 ካ/ሜ በገብርፃዲቅ ጨርቆስ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለውበባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 9,833,325 (ዘጠኝ ሚሊዬን ስምንት መቶ ሰላሳ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ አምስት ብር ሳንቲም) ሆኖ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቅያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም። ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ03/01/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4ኛ ብር 2,833,325 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰላሳ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል።የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።አሁን የሚሸጠው በፍ/ስ/ስ/ቁ/428 (1) መሰረት ነው።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት