Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የሰብል ማጨጃና መውቂያ ማሽኖች ማለትም Maize /com sheller/ እና multi Crop thresher ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም በጀርመን መንግስት የበጀት ድጋፍ የሚደገፈው በKEW-CSA ፕሮጀክት ጸድቆ የተላከ ስለሆነ ለፕሮግራሙ ተጠቃሚ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የሰብል ማጨጃና መውቂያ ማሽኖች ማለትም Maize /com sheller / እና multi Crop thresher ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺሀ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጀናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚገዛው የሰብል ማጨጃና መውቂያ ማሽን ግዥ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ እና ማቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዕቃ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከተለው የአንድ ፖስታ ስርአት በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች የቴክኒካል፣ የፋይናንሻል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪ ያውን በአንድ ላይ በማድረግ በሁለት ፖስታዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ በግልጽ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዘወትር በስራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 058 220 5849/058 320 8095/በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
10. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው እና በጨረታ ሰነዱ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የግብርና ቢሮ