Your cart is currently empty!
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ከፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በበጀት ዓመቱ ዕቅድ መሠረት ድርጅቱ በሚሠራባቸው የፕሮጀክት አካባቢዎች ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስተዳደር) ለሚገኙ የማኅበረሰብ አካላት አገልግሎት የሚውል የውሃ ጉድጓድ ( Shallow well) እና ሲዳማ ክልል፤ ዳራ ኦቲለቾ ወረዳ 1 hand dug well) ብቁ የሆኑ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች ደረጃቸው WWC-5/GC-5 ወይም ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድና የታደሰ የዋና ምዝገባ ፈቃዳቸውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት፣ በጨረታ እንድትሳተፉ ለዘመኑ በጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል የምስክር ወረቀት እና ቲን ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡30 ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ ዲላ በሚገኘው ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት ሂሳብ ክፍል በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ሁለት 2 ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ (ፖስታ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% (ሁለት በመቶ) ሲፒኦ በሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ስም ተሠርቶ በኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ውስጥ በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከአስረኛው /10ኛው/ ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
4. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-331-0049/046-331-42-33 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅና መረዳት ይቻላል፡፡
አድራሻ፡ ዲላ ከተማ ከዲላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል 100ሜትር ገባ ብሎ፡፡
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ