በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት Underground Copper Cable 3*300/150 Mm2 የሆነ በመሬት ውስጥ የሚቀበር የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት Underground Copper Cable 3*300/150 Mm2 የሆነ በመሬት ውስጥ የሚቀበር የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተፈላጊ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ።

  1. በኤሌክትሪክ እቃዎች ሽያጭ እና አቅራቢነት ሥራ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ (Trade License) ያላቸው መሆን እና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2.  በታክስ እና  (VAT) የተመዘገቡ መሆን እና የታክስ ከፍያ ክሊራንስ ማስረጃ (Tax Clearance) ማቅረብ አለባቸው።
  3. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት (Certificate of Registration) ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 50,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በCPO ወይም በባንክ የተመሰከረለት ጋራንቲ ወይንም ቢድ ቦንድ (Bid bond) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታ ሰነድ ከአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢሮ ግዢና ከፍያ ፋይናንስ ክፍል በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት/ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይቻላል።
  7. የጨረታ ሰነዱ በስም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ፖስታ ወይንም ኤንቨሎፕ ሁሉም ላይ ፊርማና የድርጅቱ፡ ማሕተም የተደረገበት በመያዝ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዢና ከፍያ ፋይናንስ ክፍል ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  8. የጨረታ መዝጊያ በዕለቱ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን ጨረታው በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባልተገኙበት አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዢና ከፍያ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ሰኞ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  9. በጨረታ ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ 10% በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
  10. ተጫራቹ ከገበያ ጥናት አማካይ ዋጋ ግምት 10% በላይና 30% በታች ያቀረበ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ፡ 046-220-8202 / 046-220 4566

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ /ሀዋሳ/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *