ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል የተለያዩ የአገልግሎት የዕቃ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢሊሊ. ኢንተርናሽናል ሆቴል 2018 . /2026 እኤአ የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ ውል በመፈራረም መስራት ይፈልጋል።

የአገልግሎት የዕቃ ግዥው አይነቶች

  • ምድብ አንድ፡የፅህፈት መሳሪያዎችና የቶነር ግዥ
  • ምድብ ሁለት፦ የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ምድብ ሶስት፡የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
  • ምድብ አራት፡የህትመት ውጤቶች
  • ምድብ አምስት፡አትክልትና ፍራፍሬዎች
  • ምድብ ስድስት፡የኬክ ግብዓት
  • ምድብ ሰባት፡የባልትና እና ቅመማ ቅመም ውጤቶች፣
  • ምድብ ስምንት፡ ስጋና የስጋ ውጤቶች
  • ምድብ ዘጠኝ፡ አሳ
  • ምድብ አስር፡ዶሮ እና እንቁለል
  • ምድብ አስራ አንድ፡የጤፍ ዱቄት
  • ምድብ አስራ ሁለት፡ግሮሰሪ የታሸጉ ምግብና የምግብ ግብዓት ግዥ
  • ምድብ አስራ ሶስት፡የአበባ አቅርቦት ግዥ፣
  • ምድብ አስራ አራት፡የቧንቧ ዕቃዎች ግዥ
  • ምድብ አስራ አምስትየአልኮል መጠጥ አቅርቦት ግዥ
  • ምድብ አስራ ስድስት፡ የቡና አቀርቦት ግዥ፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ቫት ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች እና የሚያቀርቡትን የዋጋ ዝርዝር ከቫት በፊት ባለው ዋጋ ጠቅሰው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለሚፈልጉት ምድብ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ በኩባንያው ፋይናንስ እና ፕሮኪዩመንት መምሪያ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከስራ አስኪያጅ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የእቃዎች እና የአገልግሎት ግዥ ሲቀርብ ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል የተፈረመ የጨረታ ሰነዶች ኮፒ የሚነበብ በሰም በታሸጉ ኤንቨሉፕ አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታ ሰነድ ከገዙ በኃላ በሆቴሉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ዝርዝሩን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ተገኝተው በም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩት ምድብ የጨረታ ማስከበሪያ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ስም 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ .. ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት ከፈት ሆኖ የካቲት 15 ቀን 2018 .. ከቀኑ 1030 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን የካቲት 16 ቀን 2018 . ዕለት ከቀኑ 830 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆቴሉ የስብሰባ አደራሽ ይከፈታል።
  7. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል

ዋናው /ቤት ካዛንቺስ ህንፃ 1 ፎቅ ጀነራል ማናጀር ቢሮ ስልክ 011 558 7777/70

ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል