የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጡ የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በሴፍቲኔት በጀት ላብቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የግልፅ ጨረታ  ማስታወቂያ

የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ለሚሰጡ የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በሴፍቲኔት በጀት ላብቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TN Number| ያላቸው
  3. የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወቅት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደእስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በሰሜን ወሎ ዞን ግዥንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾት አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገጽ ማህተም ማድረግና መፈረምይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግሥት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100/አንድ መቶ ብር /በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ/መጫረቻ ሰነድ ከ30/5/2018 እስከ 14/6/2018 ዓ.ም ድረስ በመምጣት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ15/6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀነ 4፡30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታቸው በሌሉበትየሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሠረት ተገዥ የመሆን /የመቀበል ግዴታ አለባቸው።
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው።
  12. የጨረታ ማስከበሪያ 25.000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን/በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል።
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል።
  14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ ስርዝ ድልዝ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 331 1597/2680 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

ማንኛውም ተጫራች ግልጽ ያልሆነለትን ነገር ደውሎ ግልጽ ካልሆነለት በስተቀር ያለአግባቡ ዋጋ መሙላት የለበትም። በኋላ ለሚያቀርበው ጥያቄ የማይቀበልና የተቋሙ ሃሳብ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እናሳስባለን።

የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *