የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የጽሕፈት መሣሪያዎች እና አይቲ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ለራሱ እና በስረ ባሉ ፑል መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት

  • ሎት 1፡- የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
  • ሎት2 – አይቲ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡

 ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ /egp/ ማያያዝ አለባቸው::

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከውጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር / ተከታታይ የሥራ ቀናት ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::

 5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1: የፅሕፈት መሣሪያዎች 1000/አንድ ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት 2፡- IT  አይቲ ዕቃዎች 10,000.00/አስር ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገm cpo ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

 6. የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ስነድ ቴክኒክ እና ፋይናንስ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከ01/አንድ /ኮፒ ጋር በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል:: ጨረታው በ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከረፋዱ 5:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተወዳዳሪዎች የሚያስገቡትን ደረጃቸውን የጠበቁ እቃዎችን ናሙና በተዘጋጀው ክፍል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-558 28 51 በመደወል መጠየቅ ይችላል፡፡
አድራሻ ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትሕ ቢሮ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግሥት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *