Your cart is currently empty!
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት የሚሆን በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለአገልግሎት የሚውል ህትመት ስራ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የህክምና ዕቃ እና መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት እና ህከምና እቃ ጥገና የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት የሚሆን በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለአገልግሎት የሚውል ህትመት ስራ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የህክምና ዕቃ እና መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፤ ህከምና እቃ ጥገና የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የሎት አይነት |
የጨረታ ማሰከበሪያ |
|
1 |
ደንብ ልብስ ስፌት |
ሎት1 |
5000 |
|
2 |
መድሀኒትና ሪኤጀንት የህክምና ዕቃ |
ሎት2 |
20000 |
|
3 |
የህክምና እቃ አመታዊ ጥገና |
ሎት3 |
4500 |
|
4 |
ህትመት |
ሎት4 |
3000 |
|
5 |
የኤሌክትሪክ እቃ |
ሎት5 |
4000 |
በዚህ መሠረት ፡
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የታደሠ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ረዳት ፋይናንስ ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በማሸግ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር )ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በጤና ጣቢያው ፋይናንስ የስራ ሂደት 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም፡፡
8. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ከተደራጁበት ወረዳ ወቅታዊ አና በአደራጃችሁ አካል እሴት መጨመራችሁን የሚያሳውቅ ደብዳቤ በአድራሻችን ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
አድራሻ ፡– ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ላፍቶ በታች ንግድ ባንክ ጀርባ ፖሊስ ጣቢያ ጎን
ስልክ 0989 166 246
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 12 ጤና ጣቢያ