Your cart is currently empty!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ምገባ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EB/EMAS/016/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በዓለም ምግብ ፕሮግራም /WFP/ በጀት ለእዳ እርታይ ወረዳ የትምህርት ቤት አገልግሎት የሚውል ምግባ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ተጋብዘዋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። እነዚህን ሰነዶች አሟልቶ ያልቀረበ ተጫራቾች በውድድሩ ሊሳተፍ አይችሉም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለአዳ አርቃይ ወረዳ የትምህርት ቤት አገልግሎት የሚውል ምግባ ቁሳቁስ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በቢሮው ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በትምህርት ቢሮ የስብስባ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 1666/ 58 320 5654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህርዳር