Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ G+ 4 የንግድ ህንፃ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Feb 08, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ስዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፤ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
|
ተቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱአይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካ.ሜ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
|
1 |
አቶ ሚኪያስ ማስረሻ ታደሰ |
አቶ ሚኪያስ ማስረሻ ታደሰ |
G+ 4 የንግድ ህንፃ |
520 ካሬ |
134/M-5 7/2007 |
በሰሜን ሸዋ ዞን ፊቼ ከተማ፤ ቀበሌ 04 |
20,740,159.43 |
መጋቢት 04 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:30-5:30- |
5:30 –6:00
|
በድጋሚ
|