የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል/ማሰልጠኛ ተቋም ለአንድ አመት ውል በመግባት የተጣራ ንቅል ስጋ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Feb 08, 2026)

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር

የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል/ማሰልጠኛ ተቋም

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል/ማሰልጠኛ ተቋም ለአንድ አመት ውል በመግባት የተጣራ ንቅል ስጋ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  2. በጨረታው ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል፣
  3. የጨረታ ሰነዱን በፖስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በግንባር ቀርቦ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አደይ አበባ ገባ ብሎበሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበርየሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  4. የሚያቀርቡት ዋጋ የአንድ ኪሎ ዋጋ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፣
  5. ጨረታው የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበየሚከፈት ይሆናል፣
  6.  ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አለሟሟላት ከጨረታው ውጭ ያስደርጋል::
  7. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ጠ መረጃ፡- 0114407460/011420235 ላይ መደወል ይቻላል::


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *