Your cart is currently empty!
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የ ቪ-ቤልት፣ ኦይል ሲል እና ቼን ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 09, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EAC 024
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የ ቪ–ቤልት፣ ኦይል ሲል እና ቼን ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
- አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በፖስታ ታሽጐ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የ ቪ–ቤልት፣ ኦይል ሲል እና ቼን ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ተፈጻሚ ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 መጠቀም ይችላሉ።
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር