ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የመኪና ጎማ እና ባትሪ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EAC 025

1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር መኪና ጎማ እና ባትሪ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የካቲት 2 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2018 . ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 230 – 630 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ 730 -1100 ድረስኢትዮ cn አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት

  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በፖስታ ታሽጐ
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፤
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች

የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች መኪና ጎማ እና ባትሪ ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን የካቲት 9 ቀን 2018 . እስከ ከጠዋቱ 430 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን የካቲት 9 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ተፈጻሚ ይሆናል

6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።

7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 መጠቀም ይችላሉ።

8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *