ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል VIRGIN POLYESTER FIBE 100,000 ኪ.ግ በሐገር ውስጥ አቅራቢዎችን (በኢትዮጵያ ብር) የሚሸጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 11, 2026)
Reporter(Feb 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር SPD18/2018-05

1. ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል VIRGIN POLYESTER FIBE 100,000 ኪ.ግ በሐገር ውስጥ አቅራቢዎችን (በኢትዮጵያ ብር) የሚሸጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይንም ከዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ፤ በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት ወይም የአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ፓፓሲኖስ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 143 ወይም 144 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ።

3. ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4. ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

5. አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን መሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር 033-5510627 / 5510211/ 0973424242 (ኮምቦልቻ) ስልክ ቁጥር 011-5530124 / 5513797/ 0970230571 (አዲስ አበባ)

ራስ ደስታ ዳምጠው ጐዳና ፓፓሲኖስ ህንፃ አንደኛ ፎቅ

የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *