Your cart is currently empty!
በአብክመ በምስ/ጎጃ/ አስ/ዞን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ ቡድን የተለያዩ እቃዎችን፣ ግንባታዎችን እና ጥገናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት፣ ለማስጠገን እና ማስገንባት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስ/ጎጃ/ አስ/ዞን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ ቡድን ለእናርጅ እናውጋ ወረዳ ለተለያዩ ሴከተር መ/ቤቶች በመደበኛ ካፒታል በጀት
- ሎት1 መንገድ ጥገና ከዋናው መስመር እስከ ኮሶ ዝራ ቀበሌ ማእክል ድረስ
- ሎት 2 መንገድ ጥገና ከዋናው መስመር እስከ ማርያም ታግባኝ ቀበሌ ማእከል ድረስ
- ሎት 3 – መንገድ ጥገና ከፈለገ ብርሀን ከተማ አስፓልት መገንጠያ እስከ ፈለገ ብርሀን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድረስ
- ሎት 4 – መንገድ ጥገና ከፈለገ ዛቸና ቀበሌ አስፓልት መገንጠያ እስከ አጃጀ ቀበሌ አስፓልት መዳረሻ ድረስ
- ሎት5 – ለደብረ ወርቅ ሆስፒታል ካርድ ክፍል ግንባታ
- ሎት 6፡– ፈለገ ዛቸና ቀበሌ ኤፍሲቲ ግንባታ እና
- ሎት7 ለምግብ አገልግሎት የሚውል በቆሎ እንዲገዛላቸው እንዲሁም ግንባታ እንዲገነባላቸው እና መንገድ እንዲጠገንላቸው በጠየቁት መሰረት ግዥ ለመግዛት ግንባታውን እና ጥገናውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት፣ ለማስጠገን እና ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡–
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ድረስ ላሉት ተወዳዳሪዎች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።
- የመንገድ ጥገና ተወዳዳሪዎች ከደረጃ RC/GC 6/ስድስት/ እና ከዚያ በላይ እንዲሁም የካርድ ከፍል ግንባታ እና ኤፍሲቲ ግንባታ ከደረጃ GC/BC 7/ሰባት/ እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚሰራው ስራ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለማንኛውም ግለሰብ በብር 100 (አንድ መቶ ብር) ሲሆን በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ በማፃፍ በነፃ ከግዥና ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት የሚቻል ሲሆን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ግን ተቀባይነት የለውም፣ የሚፃፈው የድጋፍ ደብዳቤ ኢንተርፕራይዝ የተደራጀበት ቀን እና ዓ.ም መጠቀስ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ) ሎት1–ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ሎት 2፡– ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሎት 3 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ሎት 4፡– 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር ሎት 5፡ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ሎት 6 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና ሎት 7 ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ፡ ገቢ በማድረግ መሂ – 1ን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርበታል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ድረስ ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ22ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4:00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን እንዲሁም ሎት 7 ደግሞ ለ15 ተከታታይ ቀናት 11፡30 ሲሸጥ ይቆይና በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው በተጠቀሰው ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፤ አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የስራ ትናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ግንባታውን ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25 % ከመሀንዲስ ግምት ዝቅ ብሎ ከሞላ coste break down እና project work schedule እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ /conformation letter አሸናፊነት ከግለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፤
- የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገባ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፣፣
- የውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና፣ CPO ፣ ጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሞላውን ዋጋ 10 በመቶ የነበረው ተሻሽሎ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል።
- ለግንባታው የሂሳብ ስሌትን በተመለከተ አርቲሜቲከ ቸክ ግዥ መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል።
- የስራ ዝርዝሩ መተርጎም ካለበት የማስተርጎሚያ ወጭ እንዲሁም ውል ለመያዝ የሚያስፈልጉ ሌሎች ወጭዎች ካሉ አሸናፊው ተጫራች መሸፈን የሚችል ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመለ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር-7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 663 0023 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
በአብክመ በምስ/ጎጃ/ አስ/ዞን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ ቡድን