የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Feb 11, 2026)

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ ባለመበት ቃልኪዳን አማረ እና በፍ/ባለዕዳ ሰለሞን መኮንን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.335082 በቀን 21/06/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ብሎክ 01 የቤቁ.704 ሆኖ ከጌትአስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የተመዘገበ ሲሆን በአሁን የፍርድ ባለዕዳ አቶ ሰለሞን መኮንን ስም የተገዛውን ሪል ስቴት የቦታ ስፋት በፕሮፖርሽን 150 ካ/ሜ የካ ቁቦሌ.10-1/27/6/11/ድ.255/16119/116459/02 የተናጥል ካርታ ያልተሰጠ የሐራጅ መነሻ 17,410,650 ( አስራ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ አስር ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.335082 በቀን 15/04/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ጨረታ 1/4ኛ 4,352,662.50( አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ከ50/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ/ም ይሸጣል።  የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *