Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ህንፃ ለቢሮ እና ለመጋዘን አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ስ.ኮ/ብግጨ/3/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በቦንጋ ከተማ የሚገኘውን ህንፃ ለቢሮ እና ለመጋዘን አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል። ህንፃው ብሮድባንድ ኢንተርኔት የተገጠመለትና ዋይፋይ የገባ፣ የውሃ አገልግሎት እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ከአስተማማኝ ጥበቃ ጋር ያለው በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፡ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርትፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ, ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቦንጋ ከተማ ቀበሌ ካይ ኬላ የቦንጋ ዩንቨርስቲ ሎጂ አጠገብ ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውስድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል። ጨረታው የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ስነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ ቁጥር 011 470-9095/ 011 442 3608/ 011 442 1312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ ቁጥር +251 93 727 6513
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን