በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህትመት ስራ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018

በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት

  • ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2. ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 3 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 4 የህትመት ስራ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት / በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ .. ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

3000 ብር

ሎት 2

ደንብ ልብስ

3000 ብር

ሎት 3

ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

20000 ብር

ሎት 4

የህትመት ሥራዎች

3000 ብር

5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 401 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።

6. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት 4 ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 410 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ጨረታው 10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በነጋታው ከጠዋቱ 230 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው።

9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. /ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20 ፐርሰንት የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለጨረታው የሰጡት ዋጋ 60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

14. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተሳታፊ የሆናችሁት የጨረታ ማስከበሪያ፣ የውል ማስከበሪያ እና የጨረታ ሰነድ በደጋፊ ደብዳቤ የምንቀበለው አምራች ድርጅት መሆነ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እና ያላቀረባችሁት እንደማንኛውም ተጫራች CPO ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

አድራሻ፡ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ ከገርጂ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ

ስልክ ቁጥር፡– 011-865-0287

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 13 ገርጂ ጤና ጣቢያ