የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ባለ110 ኪሎዋት ጀኔሬተር ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

የጀኔሬተር ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ባለ110 ኪሎዋት ጀኔሬተር ግዥ በሰነድ ላይ ባለው መስፈርት መሰረት በዘርፉ ላይ ከታሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረተው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፣

  1. ተጫራቾች በዚህ የሥራ ዘርፍ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ቲን ቫት፤ የንግድ መዝገባ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ.የተ አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ከ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦግ/ህ/ሥ/ማ/ፌ የግዥ ከፍል በመገኘት ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ ሲፒኦ ከጨረታ መከፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በታሸገ ፖስታ(ኤንቨሎፕ) የድርጅቱን መሃተም በመምታት ከዶከመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
  4. የሁለት አመት ኦዲት ሪፖርት 2016 እና 2017 ማቅረብ የሚችል እና አምስት ሚልዬን (5,000,000) የሚያሳይ ባንክ እስቴትመት ማቅረብ የሚችል።
  5. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ እና የፋይናንሽያል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ የድርጅቱን መሃተም በመምታት ለየብቻ በታሸገ ፖስታ(ኤንቨሎፐ) በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ22ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል።
  8. የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
  9. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
  10. ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን።
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACT ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12

ስልክ፡- 0910645442

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት

ፌዴሬሽን ኃ/የተ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *