የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ፦ ሚካኤል ገነነ እና በፍርድ ባለዕዳ ፦ ብርሃኑ ጉተማ እና በጣልቃ ገብ ንፂህት ወዳጄ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ በፍርድ አፈጻጸም ሂደት ላይ ባለው ክርክር መሠረት፣ በፍርድ ባለ ዕዳ ወይዘሮ መሠረት እሸቱ ደምሴ ስም በዲባዩ ክፍለ ከተማ፣ ደከ ቦራ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ፣ የካርታ ቁጥር KM2-306 (ወይም የቀድሞ ካርታ ቁጥር Bl/19285/16) የሆነ እና የይዞታ መለያ ቁጥሩ 0R00303091205016 ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት፤ የቤቱ መነሻ ዋጋ ብር 2,227,923.58 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሃምሳ ስምንት ሳንቲም) ሆኖ ተለይቷል መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከ05/06/2018 እስከ 05/07/2018 ድረስ ለጨረታ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ፣ በ 06/07/2018 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ በኮሚቴ አማካኝነት ስለሚሸጥ ተጫራቾች የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ (አንድ አራተኛ) ወይም 25% በሲ.ፒ.ኦ (CPO) በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት ስም በማስያዝ እንዲወዳደሩ የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *