በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ እና የተለያዩ የአትክልት ዘሮች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 14፤ ባለ16 እና ባለ20
  • ሎት 02 የተለያዩ የአትክልት ዘሮች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

 ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሉ የሚገለጽ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ

2. የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3 የግዥው መጠን ብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ እና አትክልት ዘር ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁጥር ለሎት 01 ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 02 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditonal Bank Guarantee)ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናንሺያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጂ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናዎችን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849/058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።

12, በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *