የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽህፈት ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 002/2018

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች /ቤት የግዥ ቡድን ሁለተኛ ዙር ግዥ 2018 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ

  • ሎት 1 ስቴሽነሪ፣
  • ሎት2 የደንብ ልብስ ግዥ፣
  • ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
  • ሎት 4 የህትመት ውጤቶች፣
  • ሎት 5 የፕሪንተር የኮምፒውተር የፎቶ ኮፒ ጥገና ከነመለወዋጫው፣
  • ሎት6 የፕሪንተር ቀለም ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ይጋብዛል፣
  1. ተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዥ አይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁባቸውን እቃዎች ሰነዳቸውን ሲያገቡ አብረው የሚወዳደሩበትን ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው፤
  4. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  5. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ብር 10000 ሎት 2 ብር 5000 ሎት 3 ብር 5000 ሎት 4 ብር 5000፣ ሎት 5 ብር 5000 ሎት 6 ብር 5000 የካ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች /ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱነ በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ፋይናሺያል ዶክመንት እና ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ ቴክኒካል ሰነድ ለብቻ የተሞላበት ዋጋ ለብቻ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማቅረብ ይነኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ሰነድ እስከ 10 ቀን ብቻ ተሸጦ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4 ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተት ተደርጐ ይወስዳል።
  10. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  11. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡መገናኛ ማራቶን ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4 ፎቅ ስልክ 0118107894

የየካ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች /ቤት