በደ/ኢ ከመንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ኢ ከመንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  • ሎት1 የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣
  • ሎት 2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ዕቀዎች በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

1. በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱና የንግድ ምዝገባ ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው።

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tin number) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት VAT ማስረጃ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፣ የታክስ ክሊራንስና ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ የድርጅት ማህተም፤ ስም፤ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ በሰነዱ ላይ በማድረግ ማቅረብ የሚችል።

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስገቡት የሎት1 የጽ/መሳሪያ 7000/ሰባት ሺህ ብር፣ ሎት 2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ብር 7000/ሰባት ሺህ ብር/፣ ዕቃዎች /10,000/ አስር ሺህ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የከፍያ ትዕዛዝ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሁለት መቶ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከኣሪ ዞን ከደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቀርቦ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. አሸናፊ ድርጅት ለሚያቀርባቸው ዕቃ የውል ማስከበሪያ ቢያንስ 10% በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ የሚችል

6. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃዎች እስከ በደ/ኢ/ከ/መንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት።

7. ተጫራቾች ባሸነፉበት ዕቃ ውል ገብተው ለማቅረብ ፍቃደኛ ባይሆኑ የውሉ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በጨረታው ህግና ደንብ መሰረት ለሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወስድ ሪፖርት ከተደረገ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ሊወስድ ይችላል።

8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም።

9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀናት በፊት መሆን አለበት።

10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው አስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው በተመሳሳይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አላቂ ዕቃ ይታሸጋል። 4፡30 ይከፈታል። ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ሌሎች አላቂ ዕቃ ይታሸጋል። 5፡30 ይከፈታል።

11. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ቫትን ጨምረው በግልጽ መሙላት አላባቸው።

12. ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት የሚያቀርቡት፦ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለእያንዳንዳቸው ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

13. ጨረታው በዚያው ቀን 4፡30 የጽ/መሳሪያ ፡ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 5፡30 ፡ ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው ሲከፈት የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም። ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦርጅናል ዶክመንቶቻቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

 መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ – በስልክ ቁጥር 09 24 63 02 60/ 09 25 14 83 17/ 09 01 55 73 48/ በመደወል መረጃ መውሰድ የምችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በኣሪ ዞን የደቡብ ኣሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *