በአብክመ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ጽ/ቤት የኮንስትራክሽን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአብክመ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ጽ/ቤት የኮንስትራክሽን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 08, 2026)

በድጋሚ የወጣ ግል  ጨረታ

ማስታወቂያ ጥር 03/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብ /ቤት ለደ//ግብርና /ቤት EU ፕሮጀክት በጀት 019 ቀበሌ አመላ ለሚገነባው መስኖ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል

  • የኮንስትራክሽን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች፤ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ በመሆኑ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(1) ነበር ያላቸው
  3. የግዥ መጠን ጥቅል ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ)ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 150,000/አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር ብቻ፣ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ወይም በጥሬገንዘብ ከመ/ቤታችን /ያዥ ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  6. የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነድ ማግኝት ይችላሉ፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250/ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  8. ማንኛውም ተጫራች  የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸኝ ፖስታ //ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ይህ ጨረታ በጋዜጣ በወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ይከፈታል።
  10. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል
  11. / ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ  ነው
  12. ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  13. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር1/ 2003 ተግባራዊ ይደረጋል።
  14. አቅርቦቱ 09 ቀበሌ አመላ መስኖ ፕሮጀክት ከሚገነባው የመስኖ ግንባታ ድረስ መሆኑ ይታወቅ ተጫራቾች፤ይህ መስኖ ፕሮጀክት ትልልቅ መኪናዎቹን የሚያስገባ መሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 033 461 0335 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአብክመ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ጽ/ቤት 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *