በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 08, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 002/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም /ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች እና የሕክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ 53 መድኃኒት ቤቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ / cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች

2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ /ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ሕንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 430 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ከፍል 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚዎስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ሕንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403

የሥራ ሰአት፡ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት ከሰዓት 700 ሰዓት እስከ 1100 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት

ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0118-27-91-23

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *