Addis Zemen (Apr 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደብማ 25/2018
በማኅበረ ቅዱሳን ደብርሃን ማዕከል የኢንቨስትመንትና ሀብት ልማት አስተዳደር ለአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ተመራቂ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል የመጽሔት ህትመት ሥራ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።
የግዥው ዓይነት የተመራቂ ተማሪዎች መጽሔት ህትመት
በመሆኑም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብርመክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው ::
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚቀርብ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና በአሐዱ ባንክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአቢሲኒያ ባንክ በአዋሽ ባንክ ወይም በዳሸን ባንክ ከተዘረዘሩት ባንኮች ውስጥ በአንዱ ባንክ በተከፈለበት በማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን ማዕከል ኢንቨስትመንትና ሀብት ልማት አስተዳደር ስም በተረጋገጥ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናን ጨምሮ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው (አሥራ አምስት) ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) ለማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን ማዕከል አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 00 27 23 37 10 90 ለማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን ማዕከል አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000 33 55 54 446 ለደ/ብርሃን ማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት በአዋሽ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 01 30 48 42 65 93 00 ከተዘረዘሩት ባንኮች ውስጥ በአንዱ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ደ/ብርሃን ከተማ ከሚገኘው ደ/ብርሃን ከሪፈራል ሆስፒታል ወረድ ብሎ ብርቄ ፔንስዮን አጠገብ አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መውሰድ ይችላሉ ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይናበባል። የመከፈቻ ቀኑ በሰምንቱ የእረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። ትክከለኛ የመከፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል። የግዥው መጠን ከብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባስቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሠረት ደ/ብርሃን አቡነ ጎርጎርዮስ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቀበሌ 02 ቅጥር ግቢ ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 011 637 58 49 ወይም 09 36 13 50 96 ወይም ጠየቅ ይችላል ።
በማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን ማዕከል
የኢንቨስትመንትና ሀብት ልማት አስተዳደር