በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ላሉት ፖሊስ ጣቢዎች በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ላሉት ፖሊስ ጣቢዎች በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 24, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር BPM 0004/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ላሎት ፖሊስ ጣቢዎች በ2018 በጀት ዓመት

  • ሎት 1 ለመዝገብ ቤት መዝገቦችን በዲጂታል ለማደራጀት የሚያገለግል Core i7 የሆነ ኮምፒዩተር ፣ Scanner /ስካነር እና Smart LED TV 65 ኢንች ቴሌቪዥን፣ 
  • ሎት 2፣ የተለያዩ ካሜራና የካሜራ ዕቃዎች ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከገጣሚው ጋር የሚያቀርብ ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች በተጨማሪ አሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውና የታደስ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

ሎት

ቁጥር

የሎት ዝርዝር

 

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1

Core i7 የሆነ ኮምፒዩተር ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከገጠማ ጋር

ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ

Scanner | ስካነር/ እና ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከገጠማ ጋር

ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ

Smart LED TV / ቴሌቪዥን ከሙሉ አክሰሰሪ እና ከገጠማ ጋር

ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ

ሎት 2

የተለያዩ ካሜራና የካሜራ ዕቃዎች ከሙሉ አክሰሰሪና ከገጠማ ጋር

ብር 50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ

4. ተጫራቾች በሎት1 እና ሎት2 መስሪያ ቤቱ በሚያቀርበው ሳምፕል ወይም ስፔሲፊኬሽን መሰረት ሲሆን በዚህ ጨረታ አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

5. ተጫራቾች ታክስን የሚከፍሉበት ክ/ከተማ የወረዳ ጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ስፔሲፊኬሽን መሰረት በጥራት ኮሚቴው ወይም በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ የሚደረግ ይሆናል።

7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳቦችን መስሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንድ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላትና የድርጅታችሁን ማህተም፤ ፊርማ፤ ሙሉ ስም፤ አድራሻቸውን እና ስልክ ቁጥር በመግለፅ አንድ ኦርጅናል እና ኮፒውን በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ማንኛውም ተጫራቾች በፖስታ የታሸገ ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 12፡30 እሰከ 11፡30 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መገናኛ 40/60 ኮንዶሚኒየም እሳት አደጋ ፊት ለፊት ያለው ሕንፃ 5ኛ ፎቅ የፋይ ግዥ ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡00 ሰዓት ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 2ኛ ፎቅ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

11. የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን / ፋይናሻል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. አሸናፊ ድርጅቶች የሥራ ትዕዛዝ ከተሰጣቸው በ5 ቀን ውል በመፈፀም በተከታታይ 10 ቀን ውስጥ ሥራውን መጀመር አለበት። በተጨማሪም መ/ቤቱ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

ለበለጠ መረጃ፡- 011-11-39- 454 ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ብለው መደወል ይችላሉ።

አዲስ አበባ ፖሊስ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *