Addis Zemen (Apr 24, 2026)
የመኖሪያ ቤት ጨረታ ማስታወቂያ
የአፈፃፀም ከሳሾች እነ አቶ ወ/አረጋይ ፉጄ 2ኛ ወ/ሮ አረዱ ክብሩ እና የአፈፃፀም ተከሳሾች ኛ አቶ ካሳሁን ሞገስ 2ኛ አቶ ሞገስ ገ/መድህን መካከል ባለው የአፈፃፀም ክስ መነሻ የ1ኛ አፈፃፀም ተከሳሽ በአቶ ካሳሁን ሞገስ ስም ተመዝግቦ ያለው በደቡብ ኢት/ያ ክልል ሶዶ ከተማ በመርካቶ ክ/ከተማ በፋና ወምባ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 3,200,000/ሶስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በሀራጅ የሚሸጥ ሲሆን ቤቱ በጨረታ የሚሸጠው በቀን 14/09/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። ቤቱን ተጫርቶ ለመግዛት የሚፈልግ ካለ ቀርቦ መጫረት የሚችል መሆኑን የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አዟል።
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ
የፍ/ር ችሎት