የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ሪጅን ለሰራተኞች የደንብ ልብስ ማሰፊያ የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ሪጅን ለሰራተኞች የደንብ ልብስ ማሰፊያ የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 02, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- የኢ/ኤ/አ ደሴ ሪጅን 09/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ሪጅን ለሰራተኞች የደንብ ልብስ ማሰፊያ የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፡-

ተ.ቁ

የዕቃዉ አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

የደበኞች አገልግሎት ኮትና ሱሪ ባለገበር

በቁጥር

350

3

ጃኬትና ሱሪ (ለቴክኒሻን)

በቁጥር

1304

5

ቱታ

በቁጥር

65

6

ገዋን

በቁጥር

136

1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ገንዘብ ብር 500.00 (አምስት መቶ ሃምሳ ብር) በኢ/ኤ/አገ/ ደሴ ሪጅን ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000151866248 በማስገባትና የባንክ ደረሰኙን ከታች በሚገኘው አድራሻ በማቅረብ መግዛት ይችላል። ደሴ ከተማ ሽል ጎልደን ጌት ሆቴል አካባቢ በሚገኘው አብደላ ህንፃ 5ኛ ፎቅ በሚገኛ የድርጅቱ ቢሮ የኢ/ኤ/አገ/ ደሴሪጅን ግዥ፣ ሎጀስቲክስ፣ ንብረት እና ፋሲሊቲ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

3.ተጫራቾች ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር ከ00/100) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመረኮዘ የባንክ ጋራንቲ (Bid Bond) ማስያዝ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች በማሟላት የጨረታ ሰነዳቸውን ጨረታው ከወጣበት ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ቀን ጀምሮ በስራ ስዓት እስከ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደሴ ሪጅን የሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ደሴ ከተማ ሸል ጎልደን ጌት ሆቴል አካባቢ በሚገኘው አብደላ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል

5. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

6. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0913209494 ወይም 0910791396 መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ሪጅን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *