ፍልውሃ አገልግሎት ደርጅት የፕሪንተር ፎቶ ኮፒ፤ ፋክስ ስካነር ጥገና እና ቀለም ሙሌት ግዥ እና የፓወር ኢንቨንተር /Power Inventor/ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፍልውሃ አገልግሎት ደርጅት የፕሪንተር ፎቶ ኮፒ፤ ፋክስ ስካነር ጥገና እና ቀለም ሙሌት ግዥ እና የፓወር ኢንቨንተር /Power Inventor/ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 11, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/ የአገልግሎት ግዥ

ፍልውሃ አገልግሎት ደርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት፡

  • ሎት1  የፕሪንተር ፎቶ ኮፒ፤ፋክስ ስካነር ጥገና እና ቀለም ሙሌት ግዥ

ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ የአገልግሎት ግዥ

  • ሎት 2 የፓወር ኢንቨንተር /Power Inventor/ ጥገና አገልግሎት

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ 2018 . ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከገንዘብናኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
  3. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ፌዴራል ፖሊስ የግል የጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  6.  እያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ እቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  8.  ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ሰለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
  9. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚስረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
  10. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
  11. የሚመረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 430 ይከፈታል።
  12. ተጫራቾች በሚመረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሺያል በተዝጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋላ። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ : ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው።
  13. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ለሎት 1 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን እንደዚሁም ለሎት 2 ድርጅቱ Specification/ ግምገማ (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር በሚያወጣው እስፔስፊክሽን ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፤ ነገር ግን ቴክኒካልና እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 0115  53 07 67/0115 15 73 37

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *