የመኖርያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የመኖርያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (May 11, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ አበበች አድማሱ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ተፈሪ መንክር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/88423 በታኅሳስ 22 ቀን 2013 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/216221 በህዳር 15 ቀን 2014 ዓ/ም በ03/10/2014 ዓ/ም በ21/2/2016 ዓ/ም በ21/10/2016 ዓ/ም በ19/2/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 የሚገኝ የቤት ቁጥር 1107 ስፋቱ 315 ካ/ሜ ላይ ያረፈ ባለአንድ ፎቅ የሆነ መኖርያ ቤት በሰሜን እነ እጥፍወርቅ ኪ/ማርያም ይዞታ፤ በደቡብ አቶ ይልማ ተከ/ዩሀንስ ይዞታ፤ በምስራቅ መንገድ፤ በምዕራብ የእጥፍወርቅ ኪ/ማርያም ቤት የሚያዋስነው አጠቃላይ ታጥሮ የተያዘው ግቢ ካርታ በእጥፍወርቅ ኪ/ ማርያም እና ተጋሪ እነ አቶ ተፈሪ መንክር (በአምስት ልጆች) ስም ያለ መሆኑ የካርታ ቁጥር ቦሌ 01/01/3/136-6424/00 የቦታ ስፋቱ 1053 ካ/ሜ ሲሆን አሁን በሐራጅ የሚሸጠው ይዞታ በዚህ ካርታ ውስጥ (ስር) መሆኑ የሚሸጠው ይዞታ እራሱን ችሎ ማህደር የሌለው እና መብት ያልተፈጠረለት ወይም ሰነድ የሌለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ 4,550,000 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C .P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ መሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *