Addis Zemen (May 11, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/19/2018
በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለኢንጌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አንድ ብሎክ ባለ አራት ከፍል ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
1. የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
2. የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GCBC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
3. የኦን ላይን E-TRADE ተመዝጋቢ መሆናቸውንና ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ክሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
4. ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5%ተቀናሽ ለማድርግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
5. በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ህጋዊ መታወቂያ ይዘው መምጣት አለባቸው
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 6፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
7. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 100000 /አንድ መቶ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
8. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልእናፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጫረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክንካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሀ) ተከታታይ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ከቀኑ 8፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
1.በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
2. ጨረታውየሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜናእሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
3. በወረዳው ወስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
4. ተውዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኃላ ቅደመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን።
ለበለጠመረጃ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 011 336 0631/146 ይደውሉ
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
መሀል አምባ