የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የዱቤ የሕክምና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የዱቤ የሕክምና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የዱቤ ህክምና የአገልገሎት ግዥ ለመፈጸም በድጋሜ

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግ../ብግጨ 9B 2018

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን 2018 በጀት ዓመት በድጋሜ ለሁለተኛ ጊዜ የዱቤ የሕክምና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሠረት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጠቅላላ ሆስፒታል ደረጃ ፍቃድ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ቲን፤ EGP (የአቅራቢ ተመዝጋቢነት) የጠቅላላ ሆስፒታል የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ ኢማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና /ቤት የግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ 60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል ፡፡ ጨረታው ግንቦት 14 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ+251911984467 ወይም +251910567578

ፋክስ 0114 421312

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *