የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አርባምንጭ ቅርንጫፍ የመ/ቤቱ ሠራተኞችን ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሕጋዊ የሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ በደረጃ 2 የተደራጁ ማኅበራትን በጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የጨረታውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000498682492 የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከጠቅላላ አገልግሎትና ንብረት አስተዳደር ሥራ ክፍል ቀርባችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።

መስፈርቶች፡-

1) በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ንግድ ሥራ ዘርፍ በደረጃ 2 የተደራጁ ማኅበራት የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ፣ የግብር መክፊያ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት እና በማኅበሩ ስም የታተመ ደረሰኝ ኮፒ ሠነድ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ካሉ ይበረተታሉ፤

2) ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ደረጃ (2)ሁለት ሆኖ ባለ45 ወንበርና ከዚያ በላይ የሚችል ሆኖ ብዛት/1/ የሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተሽከርካሪ መሆን አለበት።

3) ማኅበሩ ለወድድር ሲቀረብ የማኅበሩን ደረጃና ብቃት የሚገልጽ ወቅታዊ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።

4) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 20,000.00/ ሃያ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።

5) የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ በአርባምንጭ ከተማው ውስጥ ባሉ በተመረጡ ፌርማታዎች ተንቀሳቅሶ በቀን ጠዋት 2 ዙር እና ከሰዓት 2 ዙር በአጠቃላይ በቀን 4 ዙር ወይም በቀን ውስጥ 50 ኪ.ሜትር ያህል ተንቀሳቅሶ አገልግሎት ለመስጠት የሚችል።

6) የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ፡- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 ሥራ ቀናት።

7) ጨረታ የሚታሸግበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ሥራ ቀን

8) ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ የማኅበሩ ከብ ማህተም እና ፊርማ መኖር አለባቸው።

9) የመወዳደርያ ሰነድ የሚቀርበው በሰም በታሸገ ፖስታ ሲሆን በተጫማሪ የማህበሩ ክብ ማህተም በፖስታው ላይ መኖር አለበት።

ማሣሰቢያ ፡-

1. አሸናፊው ተጫራች ከተረጋገጠ በኋላ የሚቀርበው ተሽከርካሪ የደረጃ (2) ብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የመድህን ዋስትና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከውል በፊት ማቅረብ አለበት።

2. የነዳጅ ፍጆታ ከአቅራቢው ማኅበር የሚሸፈን ሲሆን የነዳጅ ዋጋው ወደ ፊት እንደ ሀገር ከፍ ያለ ዋጋ ጭማሪ ከመጣ በወቅቱ ከነበረው ዋጋ ልዩነት በንጽጽር ተሰልቶ የሚከፈል መሆኑን እናሳስባለን።

3. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማኅበር ጎን።
ስልክ ቁጥር:
046 181 1273/ 046 181 0380/ 046 181 0614/ 046 181 0539
046 181 0426 ስራ አስኪያጅ
046 181 0739 መጋዘን አያያዝ እና ክምችት አስተዳደር
እባክዎ መልስ ሲሰጡ የኛን ደብዳቤ ቁጥር ይጥቀሱ
ፖስታ ሳ.ቁ 2168
አርባምንጭ ቅርንጫፍ
epsaamb@gmail.com / www.epss.gov.et  

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *