የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮ እና በቢሮው ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮ እና በቢሮው ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለቢሮ እና በቢሮው ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 Forklift መኪና፣
  • ሎት 2 የአንቡላስ መኪና እቃዎች ፣
  • ሎት 3 የፅህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት 4 የህክምና መሳሪያ እና
  • ሎት 5 የፅዳት እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን

መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/የሚያቀርብ።

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት

4. ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1 ( Forklift መኪና) ብር 12 100,000/አንድ መቶ ሺህ/፤ ለሎት 2 ( የአንቡላስ መኪና እቃዎች) ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ፣ ለሎት 3 (የፅህፈት መሳሪያ) ብር 50,000/ሀምሳ ሺህ፤ ለሎት4 የህክምና መሳሪያ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ እና ለሎት 5 የፅዳት እቃዎች /100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፣በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ።

6. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 8፡30 ስዓት ድረስ በጤና ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል/ በ16ኛው ቀን በ8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

8. የህክምና መሳሪያ እና Forklift መኪና ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

10. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

11.የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጭ ክልል ጤና ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት።

12.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ግዥ የማይመለስ በብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክተር ክፍል ቁጥር 06 ድረስ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል።

13.ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የአብክመ ጤና ቢሮ

ባህርዳር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *