Be'kur (May 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአዘዞ ጤና ጣቢያ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውስን ጨረታ መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አዘዞ ጤና ጣቢያ ግዥ/ፋ/አስተ/ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግንቦት 03/2018 እስከ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም በተዘጋጀው በጨረታ ሣጥን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ መገኘት ካልቻሉ ጨረታው ሰዓቱን ጠብቆ የሚከፈት ይሆናል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን አንድ ወጥ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከፖስታውና ከእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
6. የእቃው መለያ ዝርዝር (ስ ፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲ ሆን ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው።
7. የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 53 60 63 /09 18 81 89 45 ደውለው በመጠየቅ ወይም አዘዞ ጤና ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስተዳደር በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ።
የአዘዞ ጤና ጣቢያ