የምእራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የቤት ሽያጭ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል – test3.diretenders.com

የምእራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የቤት ሽያጭ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል


Be'kur (May 11, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ ታሪኩ ጋሹ እና በፍ/ባለእዳ አቶ አዝመራው አንዷለም መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ጉዳይ፤ የባለእዳው ንብረት የሆነው በቁጭ ከተማ ቀበሌ 01 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ በምስራቅ ደሴ አባተ፣ በምእራብ መንገድ፣ በሰሜን ዘለቀ አንለይ እንዲሁም በደቡብ ዝናሽ መለሰ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው ፤200 ካ.ሜ ቤት፤ የግምቱ መነሻ ዋጋው ብር 984‚349 (ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት ሽህ ሶስት መቶ አርባ ዘጠኝ ) ሆኖ፤ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ የባለእዳውን ንብረት መግዛት የምትፈልጉ ከላይ በተጠቀሰው ሰአት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ አሸናፊው እንደታወቀ፤ የሽያጭ ገንዘብ ውስጥ ከተቻለ ሙሉ ክፍያውን ካልተቻለ ¼ኛውን በምእራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል።

የምእራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *