Be'kur (May 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አማካይነት ከማ/ሰቡ እና ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች በተገኘ በጀት ጅ+3 ግንባታ ግራውንዱን ለማሰራት የግንባታ ማቴራል በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እስት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
5. የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 3/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
6. የግንባታ ማቴሪያል ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየው በሎት ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከግንቦት 03/2018 እስከ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ።
9. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን እስከ በግንቦት 16/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግንቦት 16/2018 ዓ/ም 3፡30 ተዘግቶ በምሥ/ደ/ወ ቆላድባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል።
11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለዉ።
12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
13. ማንኛዉም ተጫራች (ተወዳዳሪ) አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በፍጥነት ዕቃውን ማለትም የግንባታ ማቴሪያሉን በፍጥነት ማቅረብ ይኖርበታል።
14. የግንባታ ማቴራሉ በባለሙያ ታይቶ የምንረከብ መሆኑን እንገልፃለን በተጨማሪም ሲሚንቶ የምንረከበው በናሙናው መሰረት ይሆናል።
15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም።
የቆላድባ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት