የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል – test3.diretenders.com

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል


Be'kur (May 11, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ 1ኛ ወ/ሮ አበባ በላይ፣ 2ኛ አቶ ሙሉዓለም በላይ፣ 3ኛ አቤልነህ በላይ፣ 4ኛ ወ/ሮ ህዝባዬሽ በላይ እንዲሁም 5ኛ ወ/ሮ ተስፋ በላይ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ዘላለም በላይ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ገንዘብ ክስ ክርክር ጉይይ የአቶ ዘላለም በላይ ንብረት የሆነው በቻግኒ ከተማ 05 ቀበሌ አዋሳኙም በምሥራቅ የመኪና መንገድ፣ በምዕራብ ሸንቲላ ወንዝ፣ በደቡብ ገበየሁ ተሰማና መንገድ እንዲሁም በሰሜን ወርቁ አለማየሁ ማሞ ተበጄ እና ሙሉአለም በላይ የሚዋስነውን ቤት 70 ዚንጎ የመኖሪያ ቤት ሲቀር

1ኛ. የሚዋስነውን ቤት 70 ዚንጎ የመኖሪያ ቤት ሲቀር 1ኛ 60 ዘንጐ የቆርቆሮ ቤት ክዳን ግምት በመነሻ ዋጋ ብር 215,722 (ሁለት መቶ አስራ አምስት ሽህ ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ብር) በማድረግ

2ኛ. 65 ዚንጎ የቆርቆሮ ቤት ግምት ብር በመነሻ ዋጋ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) በማድረግ

ከግንቦት 3/2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ/ም በጋዜጣ በማዋል የጨረታ አሸናፊውም 1/4ኛውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በከፍ/ፍ/ቤት በኢትዬጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000289092513 ገቢ አድርጋችሁ በማስያዝ በሰኔ 04/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችል መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ፍ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *