Addis Zemen (May 31, 2026)
የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T618
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሚገኙ አምስት (5) ለተለያዩ አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በገቢ መጋራት አሰራር በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
እነዚህም የኤርፖርት ምቹ የችርቻሮ መሸጫ ሱቅ ፣ የራስንት አልግሎት ፣ ብራንድ ፋሽን ምርቶች እና የጌጣጌጥ ሱቅ ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና ጁስ ካፌ እና ሚኒማርኬት ሱቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለማቅረብ ፈቃደኛ እንዲሁም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ተጫራች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና የግብር ከፋይነት ለ ቁጥር ያላቸው ፤ በግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋግጫ ማቅረብ የሚችሉ ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
2. ለራስቶራንት አገልግሎት እና ለአትክልት፣ ፍራፍሬ እና ጁስ ካፌ ቢያንስ ሶስት (3) ዓመት እና ከዛ በላይ የሰሩ መሆን ሲኖረባቸው ለኤርፖርት ምቹ የችርቻሮ መሸጫ ሱቅ ፣ የብራንድ ፋሽን ምርቶች እና የጌጣጌጥ ሱቅ፣ ሚኒማርኬት ሱቅ የሚጫረቱ ተጫራቾች ደግሞ ሁለት (2) ዓመት እና ከዛ በላይ የሠሩ መሆን አለባቸው፡፡
3. ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወይም የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ካላቸው ኩባንያዎች ጋር ሕጋዊ የፍራንቻይዚንግ (Franchising ) ስምምነት በማድረግ ምቹ የችርቻሮ ሱቅ (Airport Convenience Retail Shop)፣ የምግብ ቤት አገልግሎት (Restaurant Service) እንዲሁም ታዋቂ የምርት ስም ያላቸው አልባሳትና መለዋወጫዎች (Brand Fashion & Accessories) በጋራ በመሥራት መሳተፍ ይችላሉ። በዚህ አግባብ የሚሳተፉ ተጫራቾች ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል የተሰጠ ሕጋዊ የፍራንቻይዝ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም ከተቋሙ ጋር የተደረገ የጋራ መግባቢያ (MOU) ወይም የውል ስምምነት ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኞ፣ ሰኔ 22 ፣2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNTT68 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ለእያንዳንዱ የቦታ ኮድ ጨረታ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
6.ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒውን እና የመወዳደሪያ ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ዋናውን እና ኮፒውን ፣ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ከፍል ማክሰኞ፣ ሰኔ 23 ፣2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4028/8025
ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡