Your cart is currently empty!
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የወታ/ተሰ/አሽ/ማስ/ትምህርት ቤት ባለው በጀት ለት/ቤቱ ዲ/መንት አመራሮችና አሰልጣኞች ሀይሩፍ (ደረጃ-1) ሰርቪስ አገልግሎት ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡– ወታ/ተሸ/አሽ/ማስ/ት/ቤት ግ001/2018
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የወታ/ተሰ/አሽ/ማስ/ትምህርት ቤት ባለው በጀት፡ 1ኛ. ለት/ቤቱ ዲ/መንት አመራሮችና አሰልጣኞች ሀይሩፍ (ደረጃ-1) ሰርቪስ አገልግሎት ኪራይ ሰነዱ ክፍል 6 ላይ በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች፡
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ለሀይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎት ሙሉ ኢንሹራንስ የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስና ቦሎ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተሟሉ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በቁጥር 6/ሐ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
3. በቁጥር 6 “ለ” በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ከፍል 6 ላይ በሒሳብ መደብ 6252 (የሀይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎት) የሚካፈሉ ተጫራቾች ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንከ ሲፒኦ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 6 “መ ” በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ተከታታይ ቀናት ተቆጥረው) በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
4. የሀይሩፍ ሰርቪስ አገልግሎቶች የሚሰጡት አዋሽ አርባ ከተማ (አፋር ክልል ከአዲስ አበባ 235 ኪ/ሜ) የሚገኘው የወታ/ተሸ/አሸ/ማስ/ት/ቤት ይሆናል፡፡
5. የወታ/ተሸ/አሽ/ማሰ/ት/ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
6. ለማብራሪያና ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡–
ሀ. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ — የወታ/ተሸ/አሽ/ማሰ/ት/ቤት ግዥ ዴስክ
ስልክ፡– 0903 350 074 ፋክስ፡-0342 407 638
ለ. ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ፡– የወታ/ተሽ/አሽ/ማሰ/ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ
ስልክ፡– 072 299 3231 ቢሮ ቁጥር፡– 13
መ. ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፡– 6/ለ/ ይመልከቱ
ሐ. ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት አድራሻ፡– የወታ/ተሸ/አሽ/ማሰ/ት/ቤት ፋይናንስ ዴስክ
ስልክ፡– 0722 993 231 / 0903 350 074
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ
የወታ/ተሸ/አሽ/ማስ/ት/ቤት
አዋሽ አርባ