በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ ሥላም ጠቅላላ ሆስፒታል የጽዳት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማፀዳት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

2 ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ ሥላም ጠቅላላ ሆስፒታል የጽዳት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማፀዳት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መወዳደር ይችላል፡፡

  1. በመ/// ሆስፒታል ቅጥር ግቢ የሚገኘውን እና አሁን በክልሉ በኩል እየተገነባ ያለው የማስፋፊያ ግንባታ የአገልግሎት መስጫ ከፍሎችና የቅጥር ግቢውን ንፅህና የሚጠብቅና የሚያፀዳ፡፡
  2. በጥቃቅን አነስተኛ ህግ በሚያዘው መሰረት የተደራጀና መረጃ ማቅረብ የሚችል በመመሪያው መሰረት ይፈጸማል፡፡
  3. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና በዘመኑ የታደሰ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ሆስፒታሉ በሚፈልገው መሰረት የተመረጠውን ከለርና ስፌት የደንብ ልብስ በስራ ሰአት በራሱ ወጭ አሟልቶ መልበስ የሚችል፡፡
  5. ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው፡፡
  6. ማንኛውም የጽዳት ዕቃዎች ስምሳሌ፡በረኪና፣ኦሞ፣ ላርጎ፣ቪም፣ድቶል የፕላስቲክ መጥረጊያ፣ መወልወያ እና ባልድና ፎጣ በራሱ ወጭ አሟልቶ ማጽዳት የሚችል፡፡
  7. በጽዳት ስራ ላይ የሠራተኞች ብዛት 12 የሚሆንና ቅዳሜ፣ እሁድ፣ የህዝብ በአላት እና የአዘቦት ቀን 24 ሰዓት ውስጥ በጽዳት ስራ ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
  8. የመጸዳጃ ቤቶች ንጽህና በመጠበቅ የሽንት ቤት መርዝ በመጠቀም መፀዳጃ ቤቶች ሽታ አልባ መደረግ አለባቸው፡፡
  9. የበረኪና አንድ ለዘጠኝ ውህደትን በመጠቀም የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን በመወልወል ንፅህናቸውን የሚጠብቅ፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች (ማህበሩ) በጽዳት ወቅት በየአገልግሎት መስጫ ክፍሎች የሚገኙትን ንብረቶች የጽዳት ሠራተኛው በእንዝላልነትና በግደለሽነት ምክንያት ለጠፋ/ለሚጠፋ/ሠነዶች ቋሚና አላቂ እቃዎች የመንግስት ሀብትና ንብረት የሚከፍልና በህግ የመጠየቅ ግዴታ አለበት፡፡
  11. በሆስፒታሉ ህግና ደንብ መሰረት ተገዥ የሆነና ሌሎች ከጽዳት ጋር የተያያዙ ስራዎችንና የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ተቀብሎ መፈፀም የሚችል፡፡
  12. ማህበሩ መድቦ በሚያሰራው የጽዳት ሠራኞች የሚፈጠር ማንኛውንም ችግር ማህበሩ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
  13. በወር ለአገልግሎትና ለጽዳት እቃዎች ግዥ መጠየቂያ ደመወዝን ጨምሮ ሊከፍለው የሚችለውን ገንዘብ መጠን በኢትዮጵያ ብር ጥቅል ድምር በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሰነድ በወር እና በአመት የሚለው ጨረታ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት አለበት፡፡
  14. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመሠ/// ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞደል 85 ማሲያዝ አለባቸው፡፡
  16. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም በተጨማሪም በተለያዩ እስኪርብቶ ጽፎ ማቅረብ የለበትም፡፡
  17. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሠነድ ላይ በመሙላት በደንብ በታሸገ ፖስታ መካነሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ዘወትር በስራ ስዓት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ዘወትር ተከታታይ 16 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ስአት ከግ///አስ//የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታው 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል ቅዳሜ እና እሁድ (በአል) ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  18. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን ከቀኑ 830 ከሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  19. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ከግ///አስ//የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09-34-37-02-54/ 09-1434-43-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የመካነሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *