Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተለያዩ ህትመቶችን እና ደረሰኞችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቶ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁ፡– ግዥ ን/ማ/አ/ጽ/ቤት
001/2018
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት መረጃን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ለማስተላለፍ እንዲቻል የተለያዩ ህትመቶችን እና ደረሰኞችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አውጥቶ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡–
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቁጥር 09 ቀርበው ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት በ3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 215 በግልጽ ሲከፈት፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች 100,000 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግለሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 215
ስልክ ቁጥር፡– 09-15-75-57-68/ 09-1500-10-86
ፋክስ ቁጥር ፡- 025-4-11-01-79
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ