Your cart is currently empty!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት (ካ.ሜ.) |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት |
የንብረቱ አይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|||
ከተማ
|
ክ/ከተማ |
ወረዳ |
ቤቁ |
|||||||||
1 |
አቶ ምሩፅ ገዛኢ አድሃና
|
አቶ ሙሉጌታ ደባልቀው
|
ጎፋ
|
አዲስ አበባ |
አቃቂ ቃሊቲ
|
9 |
— |
506 ካ/ሜ |
023671/1 |
G+4+ቴራስ የሆነ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ
|
71,696,617.93
|
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
2 |
አቶ ሰለሞን ሀይሉ ገ/ዮሐንስ
|
አቶ ሰለሞን ሀይሉ ገ/ዮሐንስ
|
የካ
|
መቐለ
|
አይደር |
— |
— |
140 ካ/ሜ |
24736/02-5185
|
የመኖሪያ ቤት
|
5,029,444.80
|
ጨረታው የሚከናወነው በመቐለ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ሰሜን ሪጅን ጽ/ቤት መስከረም 20 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
3 |
አቶ አፈወርቅ ተክለሃይማኖት ገብረሊባኖስ
|
አቶ አፈወርቅ ተክለሃይማኖት ገብረሊባኖስ
|
አትሌት ሃይሌ
|
አዲጉደም
|
ቀበሌ 3 |
— |
— |
80,000 ካ/ሜ |
0951/10 |
ለኢንዱስትሪ የሚሆን ይዞታ
|
58,167,868.45
|
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ አዲጉደም ቅርንጫፍ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ |
4 |
አቶ አፈወርቅ ተክለሃይማኖት ገብረሊባኖስ
|
አቶ አፈወርቅ ተክለሃይማኖት ገብረሊባኖስ
|
አትሌት ሃይሌ
|
አዲግራት |
ቀበሌ 4 |
— |
— |
250 ካ/ሜ |
8319/2002 |
የመኖሪያ ቤት
|
2,603,551.06
|
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ አዲግራት ቅርንጫፍ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
5 |
ወ/ሮ ኣልማዝ ሃይሉ ለማ
|
ወ/ሮ ኣልማዝ ሃይሉ ለማ
|
ዓዲሓዉሲ |
መቐለ
|
ሓድነት
|
ዲያስፖራ |
— |
250 ካ/ሜ |
54572/05/8099 |
የመኖሪያ ቤት
|
18,055,556.86
|
ጨረታው የሚከናወነው በመቐለ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ሰሜን ሪጅን ጽ/ቤት መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
6 |
ወ/ሮ ኣልማዝ ሃይሉ ለማ
|
ኣቶ ገ/ኪዳን ኣማረ
|
ዓዲሓዉሲ |
መቐለ
|
ሓድነት
|
ስምረት |
— |
250 ካ/ሜ |
76387/05/20987 |
የመኖሪያ ቤት
|
22,374,023.59
|
ጨረታው የሚከናወነው በመቐለ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ሰሜን ሪጅን ጽ/ቤት መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
7 |
ኣቶ ገብረሂወት ከበደ የዕብዮ
|
ኣቶ ገብረሂወት ከበደ የዕብዮ
|
የጭላ |
የጭላ |
የጭላ |
መአረይ |
— |
250 ካ/ሜ |
8005/004/መ/ም/ማ/013 |
የመኖሪያ ቤት |
1,252,650.27 |
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ የጭላ ቅርንጫፍ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በተመለከተ በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚካሄደው 22 አካባቢ በሚገኘው ሌክስ ፕላዛ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይሆናል። በተ.ቁ 2-7 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚካሄደው ንብረቶቹ በሚገኙበት ከተማ ባለው የባንኩ ቅርንጫፍ ወይም መስሪያ ቤት ይሆናል።
- የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው በጠዋቱ ክፍለጊዜ 4፡00 – 5፡30 ድረስ ይሆናል። ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል።
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የእነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን።
- ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
- ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው ያልተከፈለ ውዝፍ የሊዝ እዳ፣ ወጪዎች፣ ግብር እና የሊዝ ክፍያ እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 011-662-7120 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.