Your cart is currently empty!
ላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር 11 (አስራ አንድ) ተሽከርካሪዎች መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ቁጥር
ተጫራቾች ድርጅታችን በጨረታ ለሚሸጣቸው 11 (አስራ አንድ) ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ለመሳተፍ ፈቅደው ስለመጡ በድርጅታችን ስም ምስጋና እያቀረብን በዚህ ሰነድ ከዚህ በታች የተገለጸውን የጨረታውን አፈጻጸም ዝርዝር መመሪያ በጥሞና ተገንዝበው የግዥ ውሳኔዎች እንዲያሳርፉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ተ.ቁ |
የተሽክርካሪው ዓይነት |
የሠሌዳ ቁጥር |
የምርት ዘመን |
ሞዴል |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
1 |
Toyota Terios |
3 -50765 |
2008 |
J211LG-GMDFW |
2234641 |
JDAJ211G001009312 |
2 |
Toyota RAV4 |
3-A04226 |
2014 |
ZSA44L-ANKXG |
3ZR-6024570 |
JTMDD9EV40-D045160 |
3 |
Chery QQ |
3-50295 |
2008 |
QQ311 |
SQR472FFG8G01801 |
LVVDB12AX8D216505 |
4 |
Chery QQ |
3-50296 |
2008 |
QQ311 |
SQR472FFG8G01914 |
LVVDB12AX8D216506 |
5 |
Chery Tiggo |
3-75788 |
2010 |
TIGO |
SQR481FCFFAM02626 |
LVVDB11B2BD032872 |
6 |
Hyundia grand i10 |
3-A40442 |
2016 |
i10 |
G4LAGM194232 |
MALA741CBHM214199 |
7 |
Hyundia grand i10 |
3-A68932 |
2018 |
Grand i10
|
G4LAJM111673
|
MALA741CBKM356764
|
8 |
TATA S.CABIN P/UP |
3-A36727 |
2013 |
TATA EXONON |
2.2LDICOR05JWYJ10857
|
MAT464049ESL00569 |
9 |
TATA S.CABIN P/UP |
3-50080 |
2008 |
207DI |
497SP27DRZ822610
|
MAT37441589L04060
|
10 |
Dump truck |
3-74692 |
2011 |
YC4BJ115-33 |
YC4BJ115-33-BJ1E8B70011 |
LGDSK9AHBH106477 |
11 |
Dump truck |
3-74693 |
2011 |
YC4BJ115-33 |
YC4BJ115-33-BJ1E8B70022 |
LGDGK9AH3BH106478 |
የጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መመሪያ፣
- ለሽያጭ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ማየት የሚቻለው በድርጅቱ የተመደበ አስጐብኚ ባለበት ከነሀሴ 14/2017 ጀምሮ እስከ ነሀሴ 26/2017 ዓ.ም. ባሉት የሥራ ቀናት ከቀኑ 7፡30 ሰአት እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ ነው።
- ተጫራች ለዚህ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ አለባቸው ይህ ሰነድ የድርጅቱ ማህተም ከሌለበት ዋጋ አይኖረውም።
- ተጫራች ለመግዛት የወሰኑትን ተሽከርካሪ ዋጋ በዚህ ሰነድ በግልጽ ማንበብ በሚቻል ጽሑፍ በአሃዝና በፊደል ሞልተው ፊርማቸውን (የድርጅቱ ከሆነ ማህተም) በማሳረፍ ማቅረብ አለባቸው።
- በግልጽ የማይነበብ እና አሻሚ ይዘት ያለው የጨረታ ዋጋ ውድቅ ያደርጋል።
- ተጫራች ለመግዛት የወሰኑትን ተሽከርካሪ ዋጋ ሲያቀርቡ በላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (lions International Trading PLC) ስም የተሰራ ጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ያካተተ መሆን አለበት።
- አንድ ተጫራች ከአንድ በላይ ተሽከርካሪዎች መጫረት ይችላል ሆኖም ለእያንዳንዱ ለሚጫረተው ተሽከርካሪ የመነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ያላያያዘ ከሚጫረተው ተሽከርካሪ መነሻ ዋጋ በታች ዋጋ ያቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ያላቀረበ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።
- ጨረታው ሰኞ ነሀሴ 26/ 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ ልክ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዣው ጨረታውን ላሸነፈ ተጫራች ከዋጋው ጋር ይያዝለታል፣ ለተሸነፈ ሲ.ፒ.ኦ. ተመላሽ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከፍሎ ተሽከርካሪውን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘውን ለአጫራቹ ድርጅት ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች እስከ ዛሬ ድርስ ከማንኛውም ዕዳ ነጻናቸው ዕዳ ቢገኝ በሻጭ ይሸፈናል።
- የባለቤትነት ስም ማዛወሪያ ክፍያ በገዢው ይሸፈናል።
- ድርጀቱ ስለተሽከርካሪዎች አሻሻጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ቅሬታ ካላቸው አቤቱታ የማቅረብ መብት አላቸው።
ለበለጠ መረጃ በስልክክ ቁጥር፡- 011-6-63-92-44/45
ላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር