Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መካከለኛ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መካከለኛ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መግዛት ይፈልጋል።
የሎት አይነት |
የCPO መጠን |
ለሎት 1 የደንብ ልብስ እቃዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች |
3000/ሶስት ሺህ ብር |
ለሎት 3 የሕትመት ስራዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 4 አላቂ የሕክምና እቃዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 6 አላቂ የጽዳት እቃዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 8 የፕላንት ማሽነሪንግ ጥገና |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 9 የህንጻ ቁሳቁስና ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎች |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 10 ቋሚ እቃዎችን |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ለሎት 11 የመስተንግዶ አገልግሎት |
3000/ሶስት ሺህ/ብር |
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለእያንዳንዱ ሎት 3000/ሶስት ሺህ/ ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በት/ቤቱ ስም ማሰራትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት እቃ ዋስትና በካሽ ወይም የውል ማስከበሪያ (BID BOND) 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ ıኛና መ/ት/ቤት ፋይናንስና ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁ.5 ዘወትር በስራ ሰዓት መጥቶ መውሰድ ይኖርበታል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችንም በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እንዲሁም CPOውን ከኦርጅናሉ ጋር በማያያዝ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መቀነስ ወይም መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ክፍል ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡
0111 26 75 10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ ፡– ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ አጠገብ ቴሌ ፊትለፊት
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05
አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መ/ደ/ት/ቤት