Your cart is currently empty!
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ የተዘረዘሩትን እቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1.የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2.የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3.የደንብ ልብስ፣
- ሎት 4.የላብራቶሪ ዕቃዎች እና የትምህርት መርጃ መሳሪያ
- ሎት 5.የተለያዩ አጋዥመፅሐፍት እና አዳዲስ ልብወለዶች
- ሎት 6.የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 7.የቢሮ ፈርኒቸር ጥገና እና የተለያዩ የኤሌክትሪክስ እቃዎች ጥገና
- ሎት 8.የህትመት ስራዎች፣
- ሎት 9.የህክምና ነክ እቃዎች
- ሎት10.መስተንግዶ፣
- ሎት11.የመኪና ኪራይ
ሲሆኑ በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት ኮልፌ ቀራኒዬ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሳይደርስ ቤቴል በ40 ሜትር ቪክትሪ ት/ቤት ፊት ለፊት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 04 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ከስራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው።
- የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ከገቢዎች ጊዜው ያላለፈ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ምዝገባ በኦላይን የተመዘገበ መሆን አለበት።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ተቋሙ ካደራጀቸው አካል የሚሰጥ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ እንዲሁም የስምና የስራ ድርሻ ቲተር እና ክብ ማህተም ያሟላ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ CPO
- ሎት 1. 25,700/ሃያ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ብር /
- ሎት 2. 14,600/ አስራ አራት ሺህ ሰድስት መቶ ብር /
- ሎት 3. 12900/አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር /
- ሎት 4 5,900/አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር /
- ሎት 5. 9,000/ዘጠኝ ሺህ ብር / ፣
- ሎት 6. 43,000 /አርባ ሶስት ሺህ ብር /
- ሎት 7. 9,000 /ዘጠኝ ሺህ ብር /፣
- ሎት 8. 4,000 / አራት ሺህ ብር /
- ሎት 9 5,000 / አምስት ሺህ ብር /፣
- ሎት10. 5,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር /
- ሎት 11. 5,600 / አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሲፒኦ / ከኦርጅናል ሰነዳችሁ ጋር ማስያዝ ይኖርባቹዋል፡፡ በተጨማሪ ሲፒኦ /CPO/ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ከተማ የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ በትክክል በመሙላት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡ እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል።
- መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበውን ከውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20%/ሃያ በመቶ መጨምር ወይም መቀነስ ይችላል።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል/ ተመላሽ አይደረግም፡
- የእቃ ማስረከቢያ ቦታ በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት ይሆናል፡፡
- በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት በሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር04 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን የሚውል ከሆነ ቀኑን አሳልፈን የሚከፈት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- የዕቃ ማጓጓዣ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 07 የጄ/ዋ/ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ 011 835 4110/0111 8340970 እና 01118354108
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Chemicals and Reagents cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx Hospitality, cttx IT and Telecom cttx, cttx Laboratory Equipment and Chemicals cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Rent cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Warehousing, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx, Tour and Travel cttx, Transit and Transport Service cttx