በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የሆቴል መስተንግዶ፣ የሻይ ቡና መስተንግዶ እንዲሁም ጭነት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዢ

  • ሎት 1፡- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት 2፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት 3፡- የጭነት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸው፤ 
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ 
  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር
  • ሎት 1፡- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ሎት 2፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ 30,000 ብር/ሰላሳ ሺህ/ ብር
  • ሎት 3፡- የጭነት አገልግሎት ግዥ 40,000 ብር/አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት።

8. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣው 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስስክ ቁጥር 047 135 5629
የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሚዛን አማን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *