Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ ከተማ አስተደደር የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች እና የስራ ሂደቶች ለ2018 በጀት ዓመት በድሬዳዋ ከተማ በዘጠኙም ቀበሌ በመዘዋወር ለሰራተኞች ከተማ ውስጥ ለሰርቪስ የሚሰጥ ደረጃ ሁለት የሆነ ሚኒባስ መኪና ህጋዊ የግል ትራንስፖርት ባለንብረቶች/ ህጋዊ ወኪሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Melekite Dire(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/አ/ን/ኢ/ቢአገ-ግጨ 0001/2018
በድሬዳዋ ከተማ አስተደደር የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች እና የስራ ሂደቶች ለ2018 በጀት ዓመት በድሬዳዋ ከተማ በዘጠኙም ቀበሌ በመዘዋወር ለሰራተኞች ከተማ ውስጥ ለሰርቪስ የሚሰጥ ደረጃ ሁለት የሆነ ሚኒባስ መኪና ህጋዊ የግል ትራንስፖርት ባለንብረቶች /ህጋዊ ወኪሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
3. በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገበ ሆኖ የምስክር ወረቀት ያለው፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለመኪና ብር 10.000.00 /አስር ሺህ/ በባንክ በተረጎገጠ ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ ከመወዳደሪያ ዋጋቸው ጋር አያይዘውና አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
5. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
6. ከአንድ ዓመት ያላነሰ መልካም ስራ አፈፃጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
7. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ እና የመጫረቻ ዋጋቸውን በመሙላት ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ግዥ ክፍል ለዚሁ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4፡00 ላይ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው በእረፍት ቀ ን ላይ ከዋለ በቀጣዩ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
9. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸውና ውል ከፈጸሙ በኋላ ወዲያውኑ ስራ መጀመር ይኖርባቸዋል፣
10. የስራ ውሉ እንዲቋረጥ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ውሉ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሰኔ 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል፣
11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
09 20 45 99 74 / 09 15 76 31 71 / 09 15 76 83 12