የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ስመኝ ደበበ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ፀሀይነሽ ሌቃ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/258472 በ24/5/2014 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/284703 በ9/9/2014 ዓ/ም በ28/11/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ አገልግሎት ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ/ኮድ 2-67089 DX የሆነ ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር በባለሙያ ግምት 800,000(ስምንት መቶ ሺህ ብር) የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በዕለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ በድጋሚ ጨረታ የግምቱን 1/4ኛ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሠርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *